 አሲምባ ውይይት መድረክ በዚህ ሳምንት ቅዳሜ የካቲት 6 ቀን 2002 ዓ/ም (February 13, 2010) የወያኔ ሥርዓት የሚፈልገውን እያገኘ ነው። ማሸነፉን ለማይጠራጠረው ምርጫ አነሆ ተቃዋሚ የተባሉትን በተለያየ መንገድ አንዲያጅቡትና በዓለም ፊት ሕጋዊነትን እንዲያጎናጽፉት በተለያየ ዘዴ እንደ መጋዣ ከብት ሊጎመርባቸው እየተሰናዳ ነው። እነሱም አላሳፈሩትም። በዚህ ሁሉ ውዥንብር ወያኔ ወደ አዲስ አበባ መገሥገሥ ከመጀመሩ በፊት ገና በዳዴ እየሄደ የሚያውቅው ኢሕአፓ ምርጫውን አስመልክቶ ማዕቀብ ብቻ መፍትሄ መሆኑን ግልጽ አድርጎ አስቀምጦ መግለጫ ካወጣ ሰንብት ብሎአል። በዚህ ዕለት ስለምርጫውና ስለ ሀገራች የፖለቲካ ሁናቴ እንዲያወያዩን የኢሕአፓ የበላይ አመራር አባላት ከመድረካችን ስለሚገኙ ወገኖች ያላችሁን ጥያቄና አስተያተት ይዛችሁ ከመድረካችን እንድትገኙ በማክበር እንጋብዛለን። ያአሲምባ ውይይት መድረክ እንደዋሺንግተን ዲሲ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ ሁለት ሰዓት ጀምሮ ይከፈታል። የአሲምባ ውይይት መድረክ የሀገራችንን የፖለቲካ ሁናቴ አስመልክቶ በሳል ሀሳቦች የሚንሸራሸሩብት ነጻ የውይይት መክረክ ነው።
|